የአብነት ትምህርት

የአብነት ትምህርት ምንነት

የአብነት ትምህርት ቤት ማለት ከአባት የተገኘ ከአበው የተወረሰ ከጥንት የነበረ ፣ የማንነት መግለጫ በራስ ቋንቋ ፣ በራስ ፊደል ፣ በራስ ስርዓት ትምህርት የሚሰጥ ከትውልድ ወደ ትውል የተላለፈ ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ፡፡ የአንድን ህዝብ የአንድን ሃገር ጥበብና እውቀት ለዚያ ህዝብና ለዚያች ሀገር ዜጐች የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ፡፡ የአብነት ትምህርት ቤት በልማድ “ የቆሎ ትምህርት ቤት በመባል በህዝባችን ዘንድ ይታወቃል ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ “ የቄስ ትምህርት ቤት “ አንዳንዶች ደግሞ “ የቤተክህነት ትምህርት ቤት “ ይሎታል” የሀይማኖት ቤት አባቶች የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻወች እና የዘመናዊ ትምህርትም መሰረቶች ናቸው ፡፡ ያም ሆነ ይህ ትክክለኛው ስያሜ “ የአብነት ት/ቤት ነው፡፡

የአብነት ት/ቤት የአንድን ሀገር ጥንታዊ ስነ-ጥበበ ፣ ስነ-ፊደል ፣ ስነ-ዜማ ፣ ስነ- ባህል ፣ ስነ-ስርዓት ፣ ሃይማኖት ፣ ታሪክ ፣ለዛ ፣ ዘዴ፣ ወግና ማዕረግ በልዩ ልዩ አቀራረብ አገር በቀል በሆኑ ሊቃውንት ፣ በአገር ቋንቋ ፣ በአገር ፊደል አገር በቀል በሆነ የአስተምሮ ስልት

በአብነት ትምህርት ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና ትምህርቶች

1.የፊደልና የንባብ ትምህርት ቤት፡- በዚህ ትምህርት ቤት ፊደል ፣ ንባብ ዳዊት እና የመጀመሪያ ደረጃ የዜማ ትምህርት ይሰጣል ፡፡ ይህም ትምህርት ቤት ፊደልን ከማስቆጠር ስለሚጀምር የቁጥርና የንባብ ትምህርት ቤት እየተባለ ይጠራል ፡፡

2.የቋንቋ ትምህርት ቤት፡- በቅኔ ቤት ግዕዝ ከአነባቡ ይሰጣል፤ ግዕዙን ወደ አማረኛ በመተርጐም ግዕዙንና አማረኛውን አስተባብረውና አዛምደው ለተማሪዎች ያስተምራሉ፡፡ ይህም ትምህርት ስነ-ጽሁፍን አገባብን ፣ ንባብን እና የንግግር ችሎታን ማሣወችን ያካትታል ፡፡

3.የዜማ ቤት ፡- በዜማ ቤት ከውዳሴ ማሪያም ዜማ ጀምሮ ለአርባአቱ ሰልስቱ ፣ በፆም ድጋው ፣ በድጋው ፣ በዝማሬና መምስዕቱ ፣ በአቆቋሙ በቅዳሴውና በሌሎችም ከዚማ ጋር የተየያዙ ትምህርቶች ናቸው ፡፡

4.የቅኔ ቤት ፡- በቅኔ ቤት የፈጠራ ችሎታ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የመረዳት ሁኔታ ፣ የአምሮን ጥበብ ህግን ተከትሎና ቋንቋን መርጦ አጋኖ ወይም አዋርዶ እንዲሁም መካከለኛ ደረጃ ሰጥቶ ሁኔታዎችን የመግለጥ ችሎታ ታሪክንና ወቅታዊ ሁኔታዎችን አገናዝቦ የማቅረብ ችሎታ ፋልስፋና የአስተሳሰብ ችሎታ ትምህር ነው፡፡

5.ትርጓሜ ቤት ፡- በዚህ ትምህርት ቤት የቅዱሳን መፅሀፋት ትርጓሜ ይሰጥበታል፡፡ ይህ ትምህርት ቤት በሀገራችን ጥንታዊ ስርአት ትምህርት ከፋተኛው የነበረ መለከት ትምህርት ነው

Scroll to Top