ደብረታቦርና ወርኃዊ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል በዓል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

“ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን:-ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ አንሥራ፡ አለ።” ማቴዎስ 17፥4

የዳርምሽታት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን ደብረታቦርንና ወርኃዊ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ቅዳሜ ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፲፭ (Samstag 19.08.2023) ከሌሊቱ 4 አንስቶ ዘወትር በምንገለገልበት /Schwarzerweg14b 64287 Darmstadt/ በማኅሌት በቅዳሴ በዝማሬ እናከብራለን።

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው እንዳለው ለእኛም በቤተክርስቲያን ከመገኘት የበለጠ ታላቅና ቅዱስ ተግባር የለምና ደብረታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሣሌ ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት በደብረታቦር በመገኘታቸው ብርሃነ መለኮቱን ምሥጢረ መንግሥቱን ገልጾላቸዋል። እኛም በቤተ ክርስቲያን ስንገኝ ደብረታቦርን ኢያሰብን ከተገኘን መንፈሳዊ ሕይወታችን ይታደስልናል። አምላክ ሆይ በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው እንበለው። ስለዚህ ሁላችሁም በቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ትሆነ ዘንድ ቤተክርስቲያናችሁ መንፈሳዊ ጥሪዋን ታቀርብላችኋለች።

Scroll to Top