የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በጀርመን የዳርምሽታት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
መዝሙረ ዳዊት ፻፳፪:፩

አመሰራረት

በሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤሊያስ መልካም ፍቃድ እና የቡራኬ ሥርዓት በ ፲፪. ፮. ፳፻፫ ዓ.ም. ወይንም እ.ኤ.አ. በ 12.06.2011 ተመሠረተ።

የሚሰጡ አገልግሎቶች

ቤተ ክርስቲያናችን የቅዳሴ፣ የጸሎት፣ የምህላ፣ የክርስትና፣ የፍትሃት፣ የጋብቻ እና የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ይሰጣል። በተጨማሪም የአብነት ትምህርት እና የአማርኛ ቋንቋ እየሰጠ ይገኛል።

የአባልነት መመዝገቢያ ቅጽ

ቤተ ክርስቲያናችን የአባልነቱ ቅጽ በትክክል ተሞልቶ ሲደርሳት አባልነትን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ትሰጣለች። ይህም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጀርመን አባል መሆንዎን ያረጋግጣል።

ቤተ ክርስቲያንችንን ለማገዝ

የቤተ ክርስቲያናችን ዋነኛ የገቢ ምንጭ ከምእመናን የምታገኛቸው ወርሃዊ መዋጮዎች፣ አስራት በኩራት፣ ስለት እና ሙዳዬ ምጽዋት ናቸው።

እምነት እና ትምህርት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ትምህርት፣ በቅዱሳን ሲኖዶስ ውሳኔ እና በቅዱስ ትውፊት ላይ የተመሰረተች ናት።

ልጆች እና ወጣቶች

ልጆች የቤተክርስቲያናችን ዋና አካል ናቸው። ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ መዝሙሮች፣ እሴቶች እና ትውፊቶች ጋር ለዕድሜ ተስማሚ በሆነ መንገድ ያስተዋውቃቸዋል። ለወጣቶች የተዘጋጁ ፕሮግራሞችም አሉ።

ወቅታዊ ዜና እና ትምህርቶች

የጭንቅ ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸው ዓመታት ሳይደርሱ። መክ ፲፪:፩

ለሕጻናት እና አዳጊዎች የሚሰጥ ሥራዓተ-ትምህርት
• አማርኛ ቋንቋ
• ትምህርተ ሃይማኖት
• ሥርዓተ-ቤተ ክርስቲያን
• መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

• ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር
• የቤተ ክርስቲያን ታሪክ
• አብነት ትምህርት

“ሕፃናት ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው”
ሉቃ ፩፰፥፩፮

ለህፃናት እና ለወጣቶች የሃይማኖት ትምህርት

አማርኛ ቋንቋ

ልጆች አማርኛን ማንበብ፣መፃፍ እና መናገር እንዲችሉ እንዲሁም በቤተክርስቲያን አስተምሮ እንዲያድጉ ትምህርት ይሰጣቸዋል።

ትምህርተ ሃይማኖት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት አስተምሮዎች፣ ምሥጢራትን እና መንፈሳዊ ሕይወትን ጨምሮ ለሕፃናት ተስማሚ በሆነ መንገድ ይማራሉ ።

የአብነት ትምህርት

የአብነት ትምህርት ሃይማኖታዊ የአገልግሎት ትምህርቶች የሚሰጡበት እና ተማሪዎች በግብረገብ እሴቶች የሚያድጉበት የቤተ ክርስቲያን ቀደምት የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች እና የቤተክርስቲያን ታሪክ በቅዱሳን እና በእምነት አርአያነት ላይ በማተኮር ለልጆች ተስማሚ በሆነ መንገድ ይማራሉ።

ክርስቲያናዊ እሴቶች እና የህይወት ችሎታዎች

ታማኝነትን፣ መከባበርን፣ ሃላፊነትን እና በጎ አድራጎትን ማሳደግ እንዲችሉ እና ክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያግዝ ትምህርት ይማራሉ።

የቤተክርስቲያን ትውፊት እና አምልኮ

ሥርዓተ ቅዳሴ፣ የጾም ጊዜ፣ በዓላትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ስረዓቶችን ይማራሉ።

ሥራዓተ ጋብቻ
0 +
ክርስትና
0 +
ፍትሐት
0 +
ማህበራዊ አገልግሎት
0 +