Dienstleistungen

የቅዳሴ እና ጸሎት ኪዳን አገልግሎት

የቅዳሴ አገልግሎት ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 6፡00 AM ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9፡30 AM ድረስ በ Shwarzer weg str14b, 64287 Darmstadt ይካሄዳል። እንዲሁምበተጨማሪም ከቅዳሴ አገልግሎት ቀደም ተብሎ የማህለት እና የኪዳን ጸሎት ይደርሳሉ። በተጨማሪም በበዓላት እና በጾም ወቅት (በዐቢይ ጾም ፣ በበዓላት ፣ ፍትሐት) የተራዘመ የአምልኮ ሥርዓቶች ይኖራሉ።

የሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት

ዕድሜያቸው 4 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ልጆች በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ----- ጀምሮ እስከ ቀኑ----- ድረስ በ Shwarzer weg str14b, 64287 Darmstadt የቃል ትምህርት እና የመዝሙር ጥናት ይሰጣል። እንዲሁም በተጨማሪ ዕድሜያቸው ከ15 አመት በላይ ለሆኑ ወጣቶቸ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ እና ሌሎች የ ቤተክርስቲያን ኮርሶች ይሰጣሉ። እንዲሁም በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የተለያዩ የክህሎት እና ዜማ መሳሪያ (በገና፣ከበሮ፣ማሲንቆ፣ ዋሽንት...ወዘተ) ሰልጠናዎች ይሰጣሉ።

የአብነት ትምህርት አገልግሎት:

የአብነት ትምህርት መማር ለሚፈልጉ ወጣቶች እንደየ ሁኔታው በአካል ወይም በ ቀጥታ (online) ይስጣል። ለክሀነት ሲበቁም አስፈላጊዉን ቅድመ ሁኔታ በማማላት የክህነት ስልጣን እንዲያገኙ ይደረጋል።

የንስሐ እና የጥምቀት አገልግሎት

ምዕመናን አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ የንሰሐ፣ የምክር እና የጥምቀት አገልግሎቶቸን ማግኘት ይቸላሉ። እንዲሁም ለአዳዲስ አማኞች ያልምንም ክፍያ የማስትማር እና የማጥመቅ አግልግሎቶችን እንሰጣለን።

የክርስትና፣ የጋበቻ፣ የተስካር፣ የቁርባን እና ለሎች አገልግሎቶች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና እና ስርአት በሚፈቀድው መሰረት አስፈላግውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያምዋሉ መእምናን አስፍላጊውን የክርስትና፣ የጋበቻ (በተክሊል ወይም በቁርባን )፣ የተስካር፣ የቁርባን (የመታሰብያ ጸሎት)፣ የፍትሀት እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን። እንዲሁም ለታመሙት ምእምናነ የጸሎት፣ የጥምቀት እና ኑዛዜን የመቀበል አገልግሎት እንፈጽማለን።

ማስታዎሻ: አገልግሎቶችን ሲፈልጉ እባክዎን የ አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም ሞልተው ይላኩልን። እንዲሁም አገልግሎቶቹን ለማግኘት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አባልነት መገለጫ የሆነው የሰበካ ጉባኤ ደብተር ሊኖር ይገባል። እንደየ አገልግሎቱም የአገልግሎት ክፍያዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

የዕለተ እሁድ መርሐ ግብር

Unsere regelmäßigen Gottesdienste finden an jedem Sonntag statt, sowie an wichtigen Feiertagen nach dem äthiopisch-orthodoxen Kalender.

Besondere Veranstaltungen sind z. B.:

  • Meskel (Fest des wahren Kreuzes)
  • Timket (Epiphanie)
  • Fastenzeiten & Osterliturgie
  • Gedenkgottesdienste
  • Gemeindetreffen & Ausflüge